በአስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ የምትገኘው ጋና በዛሬው እለት ምርጫ እያካሄደች ነው በአስርት ዓመታት ውስጥ የታየ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታ ሀገራዊ እዳዋን ለመክፈል የተሳናት ጋና፤ ኢኮኖሚዋ እንዲያገግም ተስፋ በመሰነቅ ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫዎችን በማካሄድ ላይ ትገኛለች። በሕገ-መንግስቱ መሠረት ለሁለት የስልጣን ዘመን ያገለገሉት ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በሚቀጥለው ወር ስልጣናቸውን ይለቃሉ። በምርጫው 12 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ዋናው ፉክክር በምክትል ፕሬዝዳንቱ እና የአኩፎ አዶ ምትክ ሆነው በተመረጡት የገዥው የአዲሱ አርበኞች ፓርቲ መሃሙዱ ባውሚያ እና ሀገሪቱን ከ2012-2016 በመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንትና የተቃዋሚው ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ኮንግረስ መካከል እንደሚደረግ በሰፊው ተገምቷል። የቅድሚያ የፓርላማ ውጤቶች እሁድ የሚጠበቁ ሲሆን ይፋዊ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት እስከ ማክሰኞ ይጠበቃል። በዓለም ሁለተኛዋ የኮኮዋ አምራች እና የወርቅ ላኪ በሆነችው ጋና፤ ከ34 ሚልዮን ዜጐች 18.7 ሚልዮን ያህሉ ለመመረጥ ተመዝግበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በአስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ የምትገኘው ጋና በዛሬው እለት ምርጫ እያካሄደች ነው
በአስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ የምትገኘው ጋና በዛሬው እለት ምርጫ እያካሄደች ነው
Sputnik አፍሪካ
በአስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ የምትገኘው ጋና በዛሬው እለት ምርጫ እያካሄደች ነው በአስርት ዓመታት ውስጥ የታየ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታ ሀገራዊ እዳዋን ለመክፈል የተሳናት ጋና፤ ኢኮኖሚዋ እንዲያገግም ተስፋ በመሰነቅ ፕሬዝዳንታዊ እና... 07.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-07T14:04+0300
2024-12-07T14:04+0300
2024-12-07T14:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በአስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ የምትገኘው ጋና በዛሬው እለት ምርጫ እያካሄደች ነው
14:04 07.12.2024 (የተሻሻለ: 14:44 07.12.2024)
ሰብስክራይብ