ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በነዳጅ ዘይት፣ ደህንነት እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙርያ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተሰማሙ

ሰብስክራይብ
ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በነዳጅ ዘይት፣ ደህንነት እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙርያ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተሰማሙ የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ተገናኝተው ተወያይተዋል። የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት፤ የአል-ቡርሃን ጉብኝት በካርቱም እና በጁባ መካከል ያለውን ትብብር ያሳድጋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሱዳን ባለስልጣናት ውይይቱ በጋራ ጉዳዮች እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረ እንደነበር ተናግረዋል። የሱዳን ልዑካን ቡድን፤ በሱዳን ጦር ሃይሎች እና በአማፂያኑ ፈጥኖ ደራሽ ሃይል መካከል ስላለው ግጭት ለፕሬዝዳንት ኪር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ የሱዳን ጦር በተለያዩ አካባቢዎች እያስመዘገባቸው ስለሚገኙ ድሎችም አንስተዋል። ውይይቱ፤ የሱዳን ኢነርጂ እና ነዳጅ ሚኒስትር እንዲሁም የሱዳን ጠቃላይ መረጃ አገልግሎት ሃላፊን ጨምሮ የሁለቱን ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያካተተ ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0