የብሪክስ የእህል ልውውጥ ፅንሰ-ሀሳብ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 እንደሚጀመር የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር አስታወቁ "ይህንን ሥራ ከጎርጎሮሳውያኑ 2025 ጀምሮ በፕሬዚዳንቱ አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን መሪነት ከኢኮኖሚ እድገት ሚኒስቴር ጋር በመሆን እንጀምራለን። የእኛ ትኩረት ሸቀጦች ላይ የተመሰረተ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ማሳደግ እንጀምራለን” ሲሉ ምንስትሯ ኦክሳና ላት በሩሲያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቻምበር ላይ ተናግረዋል።አክለውም "እስክ ጎርጎሮሳውያኑ 2025 ከሁሉም ሀገራት ጋር የሚስማማ ሂደት እንጀምራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ረጅም ሂደት ይሆናል” ብለዋል።ሚኒስትሯ የእህል ልውውጥ ፅንሰ-ሀሳብ ላይ የንግድ ማህበረሰቡን ሀሳብ እንዲሰበስብ ለቻምበሩ ሀሳብ አቅርበዋል።በጥቅምት ወር በካዛን በተካሄደው የብሪክስ ጉባዔ ወቅት የቡድኑ አባል ሀገራት የጋራ የእህል ልውውጥ ለመፍጠር ተስማምተዋል፤ ይህም በዓለም ላይ ላሉት ትልልቅ አምራቾችና ሸማቾች አዲስ የንግድ መድረክ ሆኖ ያገለግላል።በስብሰባው ወቅት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በርካታ የብሪክስ ሀገራት በእህል፣ ጥራጥሬና በቅባት ዘር ምርት መጠን በዓለም ላይ መሪ ናቸው ብለዋል። ስለዚህ የቡድኑ የእህል ልውውጥ መከፈት የዓለም አቀፍ የእህል ዋጋዎች ትክክለኛ አመላካቾች ለመፍጠር ይረዳል ሲሉም ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የብሪክስ የእህል ልውውጥ ፅንሰ-ሀሳብ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 እንደሚጀመር የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር አስታወቁ
የብሪክስ የእህል ልውውጥ ፅንሰ-ሀሳብ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 እንደሚጀመር የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር አስታወቁ
Sputnik አፍሪካ
የብሪክስ የእህል ልውውጥ ፅንሰ-ሀሳብ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 እንደሚጀመር የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር አስታወቁ "ይህንን ሥራ ከጎርጎሮሳውያኑ 2025 ጀምሮ በፕሬዚዳንቱ አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን መሪነት ከኢኮኖሚ እድገት ሚኒስቴር ጋር... 06.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-06T20:22+0300
2024-12-06T20:22+0300
2024-12-06T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የብሪክስ የእህል ልውውጥ ፅንሰ-ሀሳብ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 እንደሚጀመር የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር አስታወቁ
20:22 06.12.2024 (የተሻሻለ: 20:44 06.12.2024)
ሰብስክራይብ