የአፍሪካ ልማት ባንክ የሞሮኮን የ2030 የዓለም ዋንጫ ጥያቄን ለመደገፍ 1 ቢሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አሳወቀ

ሰብስክራይብ
  የአፍሪካ ልማት ባንክ የሞሮኮን የ2030 የዓለም ዋንጫ ጥያቄን ለመደገፍ 1 ቢሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አሳወቀሐሙስ በራባት በተካሄደው የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ  የ350 ሚሊዮን ዩሮ (370 ሚሊዮን ዶላር) የብድር ስምምነት በሞሮኮ መንግስት እና በአፍሪካ ልማት ባንክ መካከል ተፈርሟል።ይህ የመጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ ለኢኮኖሚያዊ አስተዳደር፣ ለውሃ መሰረተ ልማት እና ለናዶር ዌስት ሜድ ፖርት የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ማሻሻያ አስተዋፅኦ ያደርጋል ሲል ባንኩ ገልጿል።የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አደሲና ባንኩ ተጨማሪ 650 ሚሊዮን ዩሮ (687 ሚሊዮን ዶላር) ብድር ለመስጠትም ግምገማ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። ይህም ሞሮኮ ከስፔን እና ፖርቹጋል ጋር በጋራ ለምታስተናግደው ለ2030 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዝግጅት የምታደረገውን የባቡር እና የአውሮፕላን ማረፊያ መሰረተ ልማት ማሻሻያዎች ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሞሮኮ የሚሰጠው አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፍ 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን 37 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ያካትታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0