ሩሲያ እና ኢትዩጵያ በአካባቢ ለውጦች ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት አጋር በመሆን ለማጠናከር ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ኢትዩጵያ በአካባቢ ለውጦች ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት አጋር በመሆን ለማጠናከር ተስማሙ ውጤታማ ከነበረው የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን (ኢአጥባ) ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ እና በኢትዩጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭገኝ ቴሬኪን ውይይት በኋላ ሀገራቱ በአካባቢ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።በዚህ አጋርነት የልምድ ልውውጥን ፣ የስልጠና ፕሮግራሞችን ፣ የብክለት እና ቆሻሻ አወጋገድን ፣ የስነ ምህዳር ጥበቃን እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በተመለከቱ ቁልፍ ጉዳዩች ላይ ለመተባበር ተስማምተዋል ።ቁልፍ እና ጠንካራ ግንኙነት የሚፈጠረው በኢአጥባ እና በሚመለከተው የሩሲያ መንግስት አካል ፣ ዘርፉ ላይ ባሉ የግል ድርጅቶች  እና የምርምር ተቋማት መሀከል ሲሆን ይህም ተግባር ተኮር የሆነ በመረጃ የተደገፈ ትብብር እንዲኖር ያደርጋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0