የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካው ጋዜጠኛ ቱክር ካርልሰን ጋር ያደረጉት ቃለ-መጠየቅ ወጥቷል በቃለ-መጠየቁ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦◾ ሩሲያ ሁኔታዎች እንዲባባሱ አትፈልግም ፤ የ"ኦርሽኒክ" ሚሳኤል ሙከራ ስታደርግ አሜሪካ እንድታውቀዉ ማድረጓ ለጉዳዩ የሰጠችውን ትኩረት ያሳያል◾ የ "ኦርሽኒክ" መተኮስን አስመልክቶ የምእራቡ አለም ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ መድረስ ካልቻለ ሩሲያ ተጨማሪ "መልእክት" መላኳን ትቀጥላለች ◾ ሩሲያ የ "ኦርሽኒክ" ሚሳኤል ሙከራን ያደረገችው በጥቅሟ የሚመጡ ከሆነ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማትመለስ ለምእራቡ አለም ለማሳያት ነው◾ የአሜሪካ መንግስት "ኦርሽኒክ" ሚሳኤል ሙከራ ከመደረጉ በፊት እንዲያውቅ ተደርጓል፤ ነገርግን በሙከራ ተኩሱ ወቅት ስለአደገኝነቱ ያየው ነገር የለም◾ ሞስኮ የምእራቡ አለም በሩሲያ ላይ የሚያስበዉን "እስትራቴጂክ ሽንፈት" ለመከላከል ማንኛውንም ነገር ትጠቀማለች◾ የተወሰኑ የኑክሌር ልውውጦች ላይ የሚደረጉ ድርድሮች ሩሲያን ወደማትፈልገው አውዳሚ ነገሮች መጋበዝ ነው◾ ሩሲያ ለአለም ሲባል ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ከመተባበር የሚያግዳት ምንም ምክንያት የለም ትላለች◾ ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር ስለሚኖር ጦርነት አታስብም አትፈልገውም ፤ እንዲህ አይነት ጦርነቶች የኒኩሌር ባህሪ ሊኖራቸው ይችላል ሰለዚህ ለሞስኮ ዋናው ነገር ማስወገድ ነው◾ ምእራባውያን ሰለ ሩሲያ የሚያወጧቸው መግለጫዎች "ቀይ መስመር" ይጎድለዋል ፦ እንዲሁም የሚለውጧቸው ነገሮች ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ስህተቶች ናቸው◾ ሩሲያ እና አሜሪካ በይፋ ጦርነት ውስጥ አልገቡም ፤ በዩክሬን እየተደረገ ያለው ቅይጥ ጦርነት ነው◾ የሚንስክ ስምምነቶችን ምእራባውያን እና ኬቭ ቢያከብሩት ኖሮ ሩሲያ አሁን ያለውን የወታደራዊ ኦፕሬሽን አትጀምርም ነበር◾ ሩሲያ ዩክሬናውያን ለማጥፋት አትፈልግም የሩሲያ ህዝቦች ወንድሞች እና እህቶች ናቸው ◾ ትራምፕ ነገሮችን ማስተላለፍ የማይወድ ጠንካራ ሰው ነው ፤ በዉይይቶች ግዜም እንደ ጓደኛ ነው፤ ይህ ማለት የሩሲያ ደጋፊ ነው ማለት አይደለምበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካው ጋዜጠኛ ቱክር ካርልሰን ጋር ያደረጉት ቃለ-መጠየቅ ወጥቷል በቃለ-መጠየቁ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካው ጋዜጠኛ ቱክር ካርልሰን ጋር ያደረጉት ቃለ-መጠየቅ ወጥቷል በቃለ-መጠየቁ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦
Sputnik አፍሪካ
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካው ጋዜጠኛ ቱክር ካርልሰን ጋር ያደረጉት ቃለ-መጠየቅ ወጥቷል በቃለ-መጠየቁ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦◾ ሩሲያ ሁኔታዎች እንዲባባሱ አትፈልግም ፤ የ"ኦርሽኒክ" ሚሳኤል ሙከራ... 06.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-06T10:35+0300
2024-12-06T10:35+0300
2024-12-06T11:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካው ጋዜጠኛ ቱክር ካርልሰን ጋር ያደረጉት ቃለ-መጠየቅ ወጥቷል በቃለ-መጠየቁ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦
10:35 06.12.2024 (የተሻሻለ: 11:04 06.12.2024)
ሰብስክራይብ