"ይሄ የዘር ማጥፋት ነው። አሁኑኑ ሊቆም ይገባዋል" ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በክልሉ የዘር ማጥፋት እየፈፀመች ነው በማለት ጋዛን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ከሰሰ

ሰብስክራይብ
"ይሄ የዘር ማጥፋት ነው። አሁኑኑ ሊቆም ይገባዋል" ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በክልሉ የዘር ማጥፋት እየፈፀመች ነው በማለት ጋዛን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ከሰሰ 300 ገፅ አካባቢ በሚሆነው ሪፖርት ሆን ተብሎ የተደረጉ ግድያዎች ፣ መጠነ-ሰፊ ውድመት እና ህዝቡን ከምድረገፅ ለማጥፋት የተደረጉ ድርጊቶችን በተጠናከረ መረጃ አስደግፎ ያቀረበ ነው። ከ ጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት 2023 ጀምሮ እየተደረገ ያለውን እረፍት አልባ አውዳሚ የጦር ዘመቻዎችን በጥልቀት የሰነደው ሪፖርቱ  " ከሰው በታች እንደሆንክ አይነት ይሰማሃል" የሚል ርእስ ተሰጥቶታል።ሪፖርቱ በጋዛ ነዋሪዎች ላይ እንዴት እረፍት አልባ የቦንብ ድብደባ ፣ ረሀብ እና በሰብአዊ እርዳታዎች ላይ የእንቅስቃሴ ገደብን በመጣል ሰዎችን የማያስኖር ሁኔታ እንደተፈጠረ ያስረዳል።የአምንስቲ ሪፖርት ከ200 በላይ ያልተፈቱ የማጭበርበር እና የሙስና ጉዳዩችንም ያካትታል ። የከፍተኛ ኦፊሰሮች ያልተገባ ባህሪም ትችት ቀርቦበታል። የእስራኤል ህዝብም ጉዳዩን አስመልክቶ ብዙ ግዜ ባወጣው መግለጫ የዘርማጥፋት  ሙከራውን ጨምሮ እነዚህን ድርጊቶች ፍትሀዊ ናቸው የማለት እንደሆነ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0