ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ እስትራቴጂክ አጋርነታቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ ተስማሙ

ሰብስክራይብ
  ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ እስትራቴጂክ አጋርነታቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ ተስማሙየሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንድሬይ ሩድንኮ እና የሰሜን ኮሪያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኪም ጆንግ ጊው ስምምነቱ ወደ ተግባር የሚለውጠው ፕሮቶኮል ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።" በስምምነቱ አንቀፅ 22 መሰረት ሁሉን አካታች የሆነው በሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ መካከል የተፈረመው የእስትራቴጂክ አጋርነት ወደ ተግባር የሚለወጥበት ፊርማ ከተፈረመበት ከጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 4 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል " በማለት መግለጫው ይነበባል ።ስምምነቱ የተዘረዘሩትን ጉዳዩች ያካትታል ፦▫ በአንዳቸው ላይ ሊሚፈፀም የሚችል የጦር ወረራ ስጋት ካለ ፦ ሊደረግ ስለሚገባው እርዳታ እና ስለሚወሰድ እርምጃ ሀገሮቹ ምክክር ያደርጋሉ▫ በአንዳቸው ላይ የጦር ጥቃት ከደረሰ ሌላኛው ሀገር በፍጥነት የጦር እና ሌሎች እርዳታዎችን ያቀርባል▫ ሀገራቱ የእርስ በእርሳቸውን ፀጥታ እና ሉአላዊነትን የሚገዳደር ስምምነት ከሌላ ሶስተኛ ሀገር ጋር ላለመፈራረም ተስማምተዋል▫ ሀገራቱ በተናጠል ድጋፍ በሚያድርጉበት ወቅት እርስ በእርሳቸው ላይ ሶስተኛ አካልን መሰረት ባደረገ መልኩ  ችግር ላለመፍጠር ተስማምተዋል ▫ ሁለቱ ሀገራት የጠፈር ምርምርን ፣ ለሰላማዊ ግልጋሎት የሚውል የኑክሌር ኃይልን እና ኤአይንን ( ሰው ሰራሽ አስተውሎት) በትብብር ለማልማት ተስማምተዋል ▫ ይህ የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ እስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ያልተገደበ የጊዜ ቆይታ ያለው ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0