በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል የኢትዮጵያን ቡና በዶንባስ ክልል ለሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች ላከ

ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል የኢትዮጵያን ቡና በዶንባስ ክልል ለሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች ላከ"ይህ ወታደሮቹን ያበረታታቸዋል፤ ሙቀትም ይሰጣቸዋል፤ በዚያ ያለው የአየር ሁኔታ እንደ አፍሪካ አይደለም” ሲል ድርጅቱ በቴሌግራም ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ ገልጿል። ፓኬጁ  የሲቪል የውጭ እርዳታ እና የባህል ልውውጥን የሚያስተዳድረውና የሩሲያ ፌዴራል መንግስት ኤጀንሲ የሆነው  ሮሶትሩድኒቼስትቮ በመላው ዓለም የሚያስተባብረው "ከእናንተ ጋር ነን" የተሰኘ ተነሳሽነት አካል ነው። በ20 አገራት የሚገኙ የሩሲያ ዳያስፖራ ተወካዮች የሙቀት አልባሳትን፣ ምግብን፣ ደብዳቤዎችን፣ የህፃናት ስዕሎችን እና የመታሰቢያ ዕቃዎችን ወደ ሩሲያ ማዕከላት ማድረሳቸውንና ከዚያ ሁሉም  ወደ ዶንባስ መላካቸውን ድርጅቱ አስረድቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0