የተወሰኑ ሀገራት የምእራቡ አለም የአየር ንብረት  ቅኝ ግዛት እየፈፀመ እንደሆነ ያምናሉ በማለት ፕሬዚዳንት ቭላድሚርፑቲን ገለፁ

ሰብስክራይብ
የተወሰኑ ሀገራት የምእራቡ አለም የአየር ንብረት  ቅኝ ግዛት እየፈፀመ እንደሆነ ያምናሉ በማለት ፕሬዚዳንት ቭላድሚርፑቲን ገለፁየሩሲያው መሪ ከአለምአቀፉ የወጣት ሳይንቲስቶች ኮንግረስ ተሳታፊዎች ጋር በትላንትናው እለት ተገናኝተዋል። ከተሳታፊዎቹ አንዱ በቅርብ ጊዜ ስለተሳተፈበት የአየር ንብረት ላይ ያተኮረ ስብሰባ ውስጥ ፦ ባለሙያዎች ለአካባቢ ጥበቃ የሚወጣውን ገንዘብ  እና የድርጊቱን ውጤታማነት አወዳድረዋል በማለት ለፕሬዝዳንቱ ነግሯቸዋል። "አብዛኛዎቹ  ከአፍሪካ  እና ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተወካዩች የምእራቡ አለም በእነርሱ አጠራር "የአየር ንብረት ቅኝ-ግዛት"  ሀሳብን እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል።  ይህው ነው፦ ቴክኖሎጂዎችን በሌሎች ሀገራት ላይ ሲጭኑ የሚጠቀሟቸው ቴክኖሎጂዎች  ውድ ቴክኖሎጂዎች (በካይ ጋዞችን የሚቀንሱ) እነርሱ መግዛት የማይችሉትን እንዲሁም ምንም አይነት እርዳታ ሳይሰጧቸው ጭምር ነው። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችንም አብረው ይጭናሉ" በማለት ፕሬዚዳንት ፑቲን ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0