ቻድ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን "ሙሉ በሙሉ ጊዜ ያለፈበት" ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠችየቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ "የቻድ ሪፐብሊክ መንግሥት በሀገራችን እና በፈረንሳይ መካከል የነበረውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ለማቋረጥ ያሳለፈውን ውሳኔ ይፋ ማድረጉን የምገልጽላችሁ በጥልቅ ስሜት እና ታላቅ ሐላፊነት ነው” ሲሉ እሁድ እለት ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል።እንደ መሪው ንግግር፤ እ.አ.አ. 1976 የተፈረመው እና በ2019 የተሻሻለው ስምምነት የጋራ ግቦችን በሀገራዊ፣ ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ አውድ ለመፍታት አቅዶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ጊዜ አልፎበታል።"ስምምነቱ በሂደት ጊዜ አልፎበታል፡፡ ሙሉ በሙሉ የድሮ ነው፡፡ የጊዜውን የደህንነት፣ ጂኦፖለቲካዊ እና ስትራቴጂካዊ እውነታዎች ወይም ሙሉ ሉዓላዊነታችን ለመግለጽ የምንጠብቀውን ሕጋዊ ግምት አያሟላም" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል፡፡ዴቢ ኢትኖ፤ የቻድ የመከላከያ እና የፀጥታ ሃይሎች ብሔራዊ ድንበሩን በመጠበቅ እና የቀጠናውን ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ አቅም እንዳላቸውም ጠቁመዋል።"የዚህ ስምምነት መቀደድ የቻድን አንድነት በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ እና የዜጎቿን ደህንነት ለማረጋገጥ፤ የቻድ የመከላከያ እና የፀጥታ ሃይሎች ትልቅ ኃላፊነት፤ ከፍተኛ ቁርጠኝነት እና ትኩረት እንዲወስዱ ሊያደርግ ይገባል" ሲሉ መሪው የተናገሩ ሲሆን፤ የስምምነቱ መቋረጥ በተግባር ምንም አይለወጥም ብለዋል፡፡ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ቻድ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን "ሙሉ በሙሉ ጊዜ ያለፈበት" ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠች
ቻድ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን "ሙሉ በሙሉ ጊዜ ያለፈበት" ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠች
Sputnik አፍሪካ
ቻድ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን "ሙሉ በሙሉ ጊዜ ያለፈበት" ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠችየቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ "የቻድ ሪፐብሊክ መንግሥት በሀገራችን እና በፈረንሳይ መካከል የነበረውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ለማቋረጥ ያሳለፈውን... 02.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-02T16:57+0300
2024-12-02T16:57+0300
2024-12-02T17:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ቻድ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን "ሙሉ በሙሉ ጊዜ ያለፈበት" ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠች
16:57 02.12.2024 (የተሻሻለ: 17:04 02.12.2024)
ሰብስክራይብ