አዲሱ የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር የተደረገው የቻጎስ ደሴት ስምምነት በገለልተኛ አካል እንዲገመገም ጠየቁ

ሰብስክራይብ
አዲሱ የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር የተደረገው የቻጎስ ደሴት ስምምነት በገለልተኛ አካል እንዲገመገም ጠየቁዩናይትድ ኪንግደም የቻጎስ ደሴቶችን ሉዓላዊነት ለሞሪሸስ ለማስረከብ እና ለሀገሪቱ ዓመታዊ የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት፤ ሆኖም በዲዬጎ ጋርሺያ ደሴት የሚገኘውን የዩኤስ-ዩኬ ጦር ሰፈር ለ99 ዓመታት የመጀመሪያ ጊዜ ይዛ እንምትቆይ የሚያስቀምጠውን የጥቅምት 23ቱን ስምምነት አስመልክቱ በፓርላማ ንግግር ያደረጉት አዲሱ ተሿሚ ናቪን ራምጎላም "እስካሁን የተደረሰውን ሚስጥራዊ ረቂቅ ስምምነት በገለልተኛ አካል እንዲገመገም ጥያቄ እንዳቀረብኩ ለምክር ቤቱ ማሳወቅ እፈልጋለሁ" ብለዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተካሄዱ ለውጦች እና በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገው ድርድር ይዘት ለአዲሱ መንግሥት ግልጽ ባለመሆኑ፤ ራምጎላም ከዩናይትድ ኪንግደም የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆናታን ፓውል ጋር ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ተገናኝተው፤ በስምምነቱ ዙርያ መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።"የድርድሩን ሁኔታ በተመለከተ ከሃገር ውስጥ ባለስልጣናት እና የውጭ የህግ አማካሪዎች ጋር ተወያይቻለሁ" ብለዋል።የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር፤ ስምምነቱን “ጥሩ ስምምነት” ሲሉ ደግፈው መናገራቸው ባለፈው ሐሙስ ተዘግቧል።"የቻጎስ ስምምነት ጥሩ ስምምነት ነው፡፡ ለዩናይትድ ስቴትስ እና ለዩናይትድ ኪንግደም በጣም አስፈላጊ የሆነውን የጦር ሰፈር ያስጠብቃል፡፡ ስምምነቱን ወደፊት እንዴት ማስኬድ እንደምንችል ከአዲሱ የሞሪሺየስ አስተዳደር ጋር እየተወያየን ነው” ማለታቸውን ሚዲያው ጨምሮ ዘግቧል፡፡ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0