የባህረ ሰላጤው ሀገራት የፍልስጤም መንግሥት ምስረታን እንደሚደግፉ ገለፁ"የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ሀገራት መሪዎች በፍልስጤም ጉዳይ ላይ ያላቸውን ጽኑ አቋም፣ ወረራው እንዲያበቃ እና ከሰኔ 1967 ጀምሮ በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ላይ ለፍልስጤም ህዝብ ሉዓላዊነት ያላቸውን ድጋፍ እና ምስራቅ እየሩሳሌም ዋና ከተማ ያደረገ ነፃ የፍልስጤም መንግሥት መመስረትን እንዲሁም ፍልስጤማውያን ስደተኞች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ዋስትና እንደሚሰጡ በድጋሚ ያረጋግጣሉ" ሲሉ የባህረ ሰላጤ የትብብር ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ጃሴም አልቡዳይዊ በኩዌት ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።የባህረ ሰላጤ የትብብር ምክር ቤት አባል ሀገራት፤ በ2026 የልሳነ ምድር ጋሻ የተሰኘ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንደሚያደርጉም ዋና ጸሃፊው በሰጡት መግለጫ ጨምረው ገልፀዋል።የባህረ ሰላጤ የትብብር ምክር ቤት አባል ሀገራት ባህሬን፣ ኩዌት፣ ኦማን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ናቸው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የባህረ ሰላጤው ሀገራት የፍልስጤም መንግሥት ምስረታን እንደሚደግፉ ገለፁ
የባህረ ሰላጤው ሀገራት የፍልስጤም መንግሥት ምስረታን እንደሚደግፉ ገለፁ
Sputnik አፍሪካ
የባህረ ሰላጤው ሀገራት የፍልስጤም መንግሥት ምስረታን እንደሚደግፉ ገለፁ"የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ሀገራት መሪዎች በፍልስጤም ጉዳይ ላይ ያላቸውን ጽኑ አቋም፣ ወረራው እንዲያበቃ እና ከሰኔ 1967 ጀምሮ በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ላይ... 02.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-02T14:27+0300
2024-12-02T14:27+0300
2024-12-02T14:34+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий