የሱዳን መሪ ለሩሲያ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት፤ አል-ቡርሃን ከሩሲያ አምባሳደር አንድሬ ቼርኖቮል ጋር ከተገናኙ በኋላ ባወጣው መግለጫ "[...] የሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት [አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን] በሱዳን መንግሥት እና ሕዝብ ስም ለፕሬዝዳንት ፑቲን እና ለሱዳን ለሚሰጡት የማያወላውል ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል" ብሏል። ሩሲያ በፀጥታው ምክር ቤት ሱዳንን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ መሻሯን በማንሳት፤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሳደግ እና ለማጠናከር የሚረዳ እና ዘርፈ ብዙ ትብብርን የሚያጎለብት ትክክለኛ አቋም ነው ሲሉ ሌተናንት ጄኔራል አል-ቡርሃን መናገራቸውን፤ ሉዓላዊ ምክር ቤቱ በመግለጫው ገልጿል። የሱዳን ምሥጋና፤ በቅርቡ እንግሊዝ እና ሴራሊዮን በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ያቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ፤ ለንደን በሀገሪቱ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እና ተጨማሪ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ሙከራ ለማከናወን የምታደርገው ጥረት ነው በማለት፤ ሩሲያ ሳትደግፈው በመቅረቷ ምክንያት የመጣ ነው። እንደ እንግሊዝ እና ሴራሊዮን ገለጻ፤ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህጎችን ለማስከበር ያለመ ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሱዳን መሪ ለሩሲያ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ
የሱዳን መሪ ለሩሲያ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ
Sputnik አፍሪካ
የሱዳን መሪ ለሩሲያ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት፤ አል-ቡርሃን ከሩሲያ አምባሳደር አንድሬ ቼርኖቮል ጋር ከተገናኙ በኋላ ባወጣው መግለጫ "[...] የሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት [አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን] በሱዳን መንግሥት... 02.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-02T13:14+0300
2024-12-02T13:14+0300
2024-12-02T13:34+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий