ትራምፕ ባይደን ለልጃቸው ሀንተር ይቅርታ ማድረጋቸውን “የፍትህ መዛባት” ሲሉ ገለፁት

ሰብስክራይብ
ትራምፕ ባይደን ለልጃቸው ሀንተር ይቅርታ ማድረጋቸውን “የፍትህ መዛባት” ሲሉ ገለፁት ፕሬዝዳንት ባይደን ከዚህ ቀደም ለልጃቸው ይቅርታ እንደማያደርጉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ሆኖም ትራምፕ በምርጫው ማሸነፋቸው የደንበኛችንን የወደፊት እጣ ፈንታ አደጋ ላይ ጥሎታል ሲሉ፤ የሀንተር ጠበቆች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ባለ 52 ገጽ አተታ አሰራጭተዋል። ትራምፕ፤ ከምርጫው በፊት ባደረጉት ንግግር ምርጫውን ካሸነፉ ለሀንተር ይቅርታ ማድረግን ውድቅ ሳያደርጉ ቀርተዋል። "ጆ ለሀንተር ያደረገው ይቅርታ ለዓመታት በእስር ላይ የሚገኙትን የጄ-6 ታጋቾችን ይጨምራል? ይህ በደል እና የፍትህ መዛባት ነው" ሲሉ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል የማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ተናግረዋል። ጆ ባይደን የአስፈፃሚ ውሳኔያቸውን በመጠቀም ከዚህ ቀደም ለልጃቸው ሀንተር ይቅርታ ያደርጉ ሲሆን፤ ይህም ክሱ ፍትሃዊ አይደለም ብለው በማመናቸው እንደሆነ ገልጸው ነበር። ሀንተር በ2017 እና 2018 ከ100,000 ዶላር በላይ ታክስ በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ተከትሎ፤ የወንጀል ክስ የተመሰረተበት የመጀመሪያው የተቀማጭ ፕሬዝዳንት ልጅ ሆኗል። በተመሳሳይ በ2018 ኮልት ሽጉጥ ይዞ ሕገ-ወጥ እፅ በመጠቀም ክስ የቀረበበት ሲሆን፤ ጥፋተኛ ከተባለ እስከ 10 ዓመት እስራት ሊተላለፍበት ይችላል። የቅጣት ውሳኔው ለታህሳስ ወር ተቀጥሯል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0