ፈረንሳይ ለጥናት የወሰደቻቸውን 3,500 የሚደርሱ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች ከአስርት ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ልትመልስ እንደሆነ ተሰማ

ሰብስክራይብ
ፈረንሳይ ለጥናት የወሰደቻቸውን 3,500 የሚደርሱ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች ከአስርት ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ልትመልስ እንደሆነ ተሰማ በብሔራዊ ሙዚየም ጉብኝት ያደረጉት የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን-ኖኤል ባሮት፤ ሁለት የእጅ መጥረቢያዎችን እና የድንጋይ መቁረጫ መሳሪያ ለአፍሪካዊቷ ሀገር ቱሪዝም ሚኒስትር ማስረከባቸውን የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ዘግቧል። ቅርሶቹ ከ1 እስከ 2 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያላቸው እና በፈረንሳዊው ፕሮፌሰር ዣን ቻቪሎን በተመራ ቁፋሮ ኢትዮጵያዊ ውስጥ እንደተገኙ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። በተደረገው ስምምነት መሰረት ቅርሶቹ ለጥናት ከአራት አስርት ዓመታት በፊት ወደ ፈረንሳይ የተላኩ ሲሆን ማክሰኞ እለት ሙሉ ለሙሉ ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እንደሚተላለፉ ተገልጿል። ግኝቶቹ በፈረንሣይ መንግሥት የቅርስ መዝገብ ውስጥ ባለመካተታቸው፤ ልውውጡ ማስተላለፍ እንጂ መመለስ እንዳልሆነ ተጠቁሟል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0