ሩሲያ እና ኒጀር በኢነርጂ እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ፤ ከኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ማሃማኔ ላሚን ዜይን እና የኒጀር ሪፐብሊክ ርዕሰ መስተዳድርና የሀገር ውስጥ መከላከያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱራህማን ቺያኒ ጋር በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ ተገናኝተው ተወያይተዋል። ሀገራቱ አንዱ ሌላውን ወሳኝ አጋር አድርገው እንደሚቆጥሩ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል። በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ በስነ-ምድር አሰሳ እና በማዕድን ክምችት ልማት ላይ ተግባራዊ ትብብርን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል። በሰብዓዊ ዘርፍ ትምህርት፣ ባህልና ስፖርትን ጨምሮ ትብብርን በማጠናከር ዙርያም መክረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቫክ፤ በቅርቡ በሴንት ፒተርስበርግ የተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ፤ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ትብብር እንዳሳደገና የኢነርጂ እና የትራንስፖርት መሠረተ ልማትን ጨምሮ፤ የህይወት ጥራትን ማሻሻል ላይ ያተኮሩ የጋራ ፕሮጀክቶች እንዲጠናከር ማድረጉን ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ እና ኒጀር በኢነርጂ እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ሩሲያ እና ኒጀር በኢነርጂ እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ኒጀር በኢነርጂ እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ፤ ከኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ማሃማኔ ላሚን ዜይን እና የኒጀር ሪፐብሊክ ርዕሰ መስተዳድርና... 30.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-30T18:23+0300
2024-11-30T18:23+0300
2024-11-30T18:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና ኒጀር በኢነርጂ እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
18:23 30.11.2024 (የተሻሻለ: 18:44 30.11.2024)
ሰብስክራይብ