ሩሲያ እና ሶሪያ በአሌፖ እና ኢድሊብ አሸባሪዎችን መመለሳቸውን እንደቀጠሉ ተገለጸ በሶሪያ የሚገኘው የሩስያ የእርቅ ማእከል፤ በአሌፖ እና ኢድሊብ ክልሎች የሩሲያ እና የሶሪያ የጋራ ኃይል የአሸባሪዎች ጥቃትን ለመመለስ እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። "የሩሲያ አየር ኃይል በሕገ-ወጥ ታጠቂ ቡድኖች፣ ኮማንድ ፖስቶች፣ መጋዘኖች እና የመድፍ ቦታዎች ላይ በሚሳኤል እና በቦምብ ድብደባ እየፈፀመ ነው። ባለፉት 24 ሰዓታት ቢያንስ 200 ታጣቂዎች ተገድለዋል። ጽንፈኞቹን ለመመከት የሚደረገው ዘመቻ እንደቀጠለ ነው” ብሏል መግለጫው። የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴርም ዘመቻውን አስመልክቶ ሪፖርት አውጥቷል። የሶሪያ ጦር የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል እና ጥቃቱን ለመመከት ክልሉን በመሳሪያ እና በወታደር ማጠናከር መቀጠሉን በመግለጫው አስታውቋል።"በደርዘን የሚቆጠሩ መኪኖች እና የጦር ተሽከርካሪዎች ወድመዋል እንዲሁም 17 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተመትተው ወድመዋል" ሲል መግለጫው ተነቧል። በአሌፖ የሚገኘው የስፑትኒክ ዘጋቢ በርካታ ተጨማሪ ኃይል መሰማራቱን አረጋግጦ፤ በምዕራብ አሌፖ አካባቢዎች ጥንቃቄ የተሞላበት እርጋታ እንደቀጠለ ተናግሯል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ እና ሶሪያ በአሌፖ እና ኢድሊብ አሸባሪዎችን መመለሳቸውን እንደቀጠሉ ተገለጸ
ሩሲያ እና ሶሪያ በአሌፖ እና ኢድሊብ አሸባሪዎችን መመለሳቸውን እንደቀጠሉ ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ሶሪያ በአሌፖ እና ኢድሊብ አሸባሪዎችን መመለሳቸውን እንደቀጠሉ ተገለጸ በሶሪያ የሚገኘው የሩስያ የእርቅ ማእከል፤ በአሌፖ እና ኢድሊብ ክልሎች የሩሲያ እና የሶሪያ የጋራ ኃይል የአሸባሪዎች ጥቃትን ለመመለስ እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ... 30.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-30T17:04+0300
2024-11-30T17:04+0300
2024-11-30T17:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና ሶሪያ በአሌፖ እና ኢድሊብ አሸባሪዎችን መመለሳቸውን እንደቀጠሉ ተገለጸ
17:04 30.11.2024 (የተሻሻለ: 17:44 30.11.2024)
ሰብስክራይብ