ሩሲያ ቡርኪናፋሶ ውስጥ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን የመገንባት አቅም እንዳላት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ቡርኪናፋሶ ውስጥ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን የመገንባት አቅም እንዳላት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ በቅርቡ በማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር የስራ ጉብኝት ያደረጉት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ፤ ቡርኪናፋሶ የኤሌክትሪክ እጥረት እንዳጋጠማት ተናግረዋል። "በቡርኪናፋሶ ውስጥ ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር ልንሰራቸው የምንችለው የጋራ ፕሮጀክቶች አሉ። የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን ለማልማት እና ለመገንባት እንዲሁም የሞዱላር ኃይል ማመንጫ አቅርቦት እድሎች አሉ" ብለዋል ኖቫክ። እንደ የሩሲያው ባለሥልጣን ገለጻ፤ ለዚህ ዓላማ የካፒታል ኢንቨስትመንቶች ጥበቃ እና የማበረታቻ ስምምነትን ጨምሮ የቁጥጥር ማዕቀፍ ይፈርማል። ሩሲያ፤ ለቡርኪናፋሶ የግብርና ምርቶችን በሰብአዊ እርዳታ መልክ ማቅረቧን እንደምትቀጥል ኖቫክ ጨምረው ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0