ጋቦን የሕዝበ ውሳኔውን የመጨረሻ ውጤት በመቀበል አዲስ ሕገ-መንግሥት አፀደቀች

ሰብስክራይብ
ጋቦን የሕዝበ ውሳኔውን የመጨረሻ ውጤት በመቀበል አዲስ ሕገ-መንግሥት አፀደቀች "91.64% መራጭ የሕገ-መንግሥቱን ረቂቅ ሲደግፍ 8.36% ተቃውሞታል [...] የምርጫ ተሳታፊዎች ቁጥር 54.18% ነበር" ያሉት የጋቦን የሽግግር ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዲዩዶኔ አባአ ኦዎኖ፤ ፍርድ ቤቱ ድምፁ እንዲሻር የሚጠይቅ አቤቱታ እንዳልደረሰው ጠቁመዋል። የተረጋገጠው የህዳር 7ቱ ህዝበ ውሳኔ ውጤት፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በጋቦን የሀገር ውስጥ እና የደህንነት ሚኒስትር ኸርማን ኢሞንጋውልት ከታወጀው ቅድሚያ ውጤት በአንድ አስረኛ ነጥብ ይለያል። የሕገ-መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ውሳኔ ይግባኝ ሊቀርብበት አይችልም። አዲሱ ሕገ-መንግሥት፤ የፕሬዝዳንቱን ሥልጣን የሚያጠናክር ሲሆን የመንግሥት ተቋማትን ሥልጣን ይቀንሳል። አንዴ ብቻ በድጋሚ የመመረጥ መብት የሚሰጥ የሰባት ዓመት የፕሬዝዳንታዊ የስልጣን ዘመን ይመሰርታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተሰርዞ ሥራው ለምክትል ፕሬዝዳንቱ ተሰጥቷል። ወታደራዊ አገልግሎት ግዴታ ሆኗል። የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የተከለከለ ነው። ፈረንሳይኛ ቋንቋ ደግሞ የስራ ቋንቋ ይሆናል። የአዲሱ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 172፤ ሕጉ የሪፐብሊኩ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ነሐሴ 2025 በሚካሄደው ምርጫ ከተመረጡ በኋላ፤ ጋቦን ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ይደነግጋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0