የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን ልማት መደገፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን ልማት መደገፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ የአፍሪካ ልማት ባንክ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በአዲስ አበባ አክብሯል። የባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ክልል ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ ሊያንድሬ ባሶል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ባንኩ የአፍሪካን ልማት ለማረጋገጥና ከድኅነት ለመውጣት የሚያግዙ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች ድጋፍ በማድረግ ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶች፣ የጤና ተቋማትንና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እውን ለማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ፤ ኢትዮጵያ ለምታከናውነው የልማት ሥራዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0