የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የአልማዝ ማዕቀብ መነሳት ሀገሪቱን ለሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች የበለጠ ሳቢ ያደርጋታል ሲሉ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የአልማዝ ማዕቀብ መነሳት ሀገሪቱን ለሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች የበለጠ ሳቢ ያደርጋታል ሲሉ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ቢካንቶቭ፤ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አስተደደር የግንባታ እና ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ሚኒስትር ተወካይ ፓስካል ቢዳ ኮያግቤሌ ጋር ተገናኝተው፤ ሀገሪቱ ላይ ተጥሎ የነበረው የአልማዝ ኤክስፖርት ገደብ መነሳቱን ተከትሎ፤ በአልማዝ ማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ዙርያ እንደተወያዩ ባንግዊ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ አስታውቋል። ኤምባሲው እንደገለጸው፤ የሩሲያ ባለስልጣናት የንግድ ክልከላውን ለማስነሳት ያደረጉትን እገዛ ያመሰገኑት ሚኒስትሩ፤ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለግዙፍ የሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች ይበልጥ ሳቢ እንደምትሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል። የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርቻን ቱአዴራ፤ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአልማዝ ኤክስፖርት ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ለማስንሳት ላደረጉት ድጋፍ ምሥጋና ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0