የህዳር 18 ምሽት ዓበይት የአለም ዜናዎች፦▫ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑትን ከካዛኪስታኑ ፕሬዚዳንት ካሰይም ጆማርት ቶካዬቭ በነበራቸው ውይይት ሞስኮ የአስታን ግዙፍ የንግድ እና የኢኮኖሚ አጋር መሆኗን ትቀጥላለች ብለዋል። በተለያዩ ዘርፎች ላይ ለሚደረጉ ድርድሮች ሰነዶች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን አስረድቷል።▫ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበርሊን የሚገኘው የሩሲያው ቻናል አንድ ቢሮ በባልስልጣናት አለመዘጋቱን ፣ የሩሲያ ጋዜጠኞች ስራቸውን መቀጠል እንደሚችሉ እና ምንአልባት ጉዳዩ ከቪዛ ጋር የተያያዘ ይሆናል ብለዋል▫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጪዎቹ ቀናት በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ከቱርክ፣ ግብፅ ፣ ኳታር ፣ እስራኤል እና ሌሎችም ጋር በመሆን እርምጃዎችን እንደሚወስዱ አስታወቁ። ▫ በውጤቱ የመጪዎቹን አመታት የፈረንሳይ የፖለቲካ አሰላለፍ ሊቀይር ይችላል የተባለ ችሎት በፓሪስ እየተካሄደ ነው። ይህ በፈረንሳይ ፖለቲከኛ ማሪን ለ ፔን እና በፓርቲዋ ላይ እየተሰማ ያለው ክስ ለአውሮፓ ፓርላማ በማጭበርበር ላይ ተመስርቶ ስለተፈፀመው የረዳቶች ቅጥር የሚያወሳ ነው። ▫ በሊባኖስ የስፑትኒክ የዜና ወኪል የሆነው አብደልካድር አል ቤይ በዛሬው እለት በእስራኤል አየር ጥቃት በእግሩ ላይ መጠነኛ ጉዳት ደረሰበት።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የህዳር 18 ምሽት ዓበይት የአለም ዜናዎች፦
የህዳር 18 ምሽት ዓበይት የአለም ዜናዎች፦
Sputnik አፍሪካ
የህዳር 18 ምሽት ዓበይት የአለም ዜናዎች፦▫ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑትን ከካዛኪስታኑ ፕሬዚዳንት ካሰይም ጆማርት ቶካዬቭ በነበራቸው ውይይት ሞስኮ የአስታን ግዙፍ የንግድ እና የኢኮኖሚ አጋር መሆኗን ትቀጥላለች ብለዋል። በተለያዩ ዘርፎች ላይ... 27.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-27T20:58+0300
2024-11-27T20:58+0300
2024-11-27T21:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий