ኬንያ ለሩሲያ ስንዴ ላኪዎች መልካም አጋጣሚ እየፈጠረች ነው በማለት በብሄራዊ ደረጃ የግብርና ምርቶች ደህንነት እና ጥራት ግምገማ ዳይሬክተር ተናገሩ " የሩሲያ ስንዴ ላኪዎች ባለፉት ጥቂት አመታት ለኬኒያ የሚያቀርቡትን ምርት አሳድገዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ 2022/23 የተላከው የስንዴ የምርት መጠን 1.1 ሚሊዩን ቶን ሲሆን በ2023/24 የግብርና አመት ወደ 1.5 ሚሊዩን ቶን አድጓል። ለ2024/25 820,700 ቶን የስንዴ ምርት ሩሲያ ወደ ኬንያ ልካለች" ያሉት በብሄራዊ ደረጃ የግብርና ምርቶች ደህንነት እና ጥራት ግምገማ ዳይሬክተር የሆኑት ሩስላን ካሃሳኖቫ ለሩሲያ የዜና ወኪል ተናግረዋል። አክለውም ኬንያ እየጨመረ ላለው የሩሲያ ስንዴ የውጭ ንግድ ተስፋ ሰጪ ሀገር ናት ብለዋል። በአጠቃላይ በ2024/25 የግብርና አመት ኬንያ 2.6 ሚሊዮን ቶን እህል ከተለያዩ ሀገራት አስገብታለች በማለት ካሃሳኖቫ አስረድተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኬንያ ለሩሲያ ስንዴ ላኪዎች መልካም አጋጣሚ እየፈጠረች ነው በማለት በብሄራዊ ደረጃ የግብርና ምርቶች ደህንነት እና ጥራት ግምገማ ዳይሬክተር ተናገሩ
ኬንያ ለሩሲያ ስንዴ ላኪዎች መልካም አጋጣሚ እየፈጠረች ነው በማለት በብሄራዊ ደረጃ የግብርና ምርቶች ደህንነት እና ጥራት ግምገማ ዳይሬክተር ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ኬንያ ለሩሲያ ስንዴ ላኪዎች መልካም አጋጣሚ እየፈጠረች ነው በማለት በብሄራዊ ደረጃ የግብርና ምርቶች ደህንነት እና ጥራት ግምገማ ዳይሬክተር ተናገሩ " የሩሲያ ስንዴ ላኪዎች ባለፉት ጥቂት አመታት ለኬኒያ የሚያቀርቡትን ምርት አሳድገዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ... 27.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-27T19:20+0300
2024-11-27T19:20+0300
2024-11-27T19:34+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኬንያ ለሩሲያ ስንዴ ላኪዎች መልካም አጋጣሚ እየፈጠረች ነው በማለት በብሄራዊ ደረጃ የግብርና ምርቶች ደህንነት እና ጥራት ግምገማ ዳይሬክተር ተናገሩ
19:20 27.11.2024 (የተሻሻለ: 19:34 27.11.2024)
ሰብስክራይብ