የሩሲያው ሮሳቶም ኩባንያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማእከል አዋጭነት ጥናት ለመስራት ኮንትራት ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ
የሩሲያው ሮሳቶም ኩባንያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማእከል አዋጭነት ጥናት ለመስራት ኮንትራት ተፈራረሙ"የሩሲያዉ መንግስት የኒኩለር ኢነርጂ ኩባንያ በሆነው ሮሳቶም አስተዳደር ስር የሚገኝ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኑክሌር ሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ማእከሎችን በኢትዮጵያ ለመገንባት የአዋጪነት ጥናት ለማድረግ ኮንትራት ተፈራርመዋል" በማለት ሮሳቶም በመግለጫው  አትቷል። ሮሳቶም በቅርቡ የሀገሪቱን ኢነርጂ ያልሆነ ዘርፍ እና የኢኮኖሚ የቴክኖሎጂ ፍላጎትን በማዕከሉ ቁልፍ  ቦታ ላይ ይገመግማል፤ እንዲሁም በማዕከሉ ላይ የተመሰረቱ የንግድ ምርቶች እና አገልግሎቶች ገበያ ለመፍጠር፣ ለማዕከሉ ቦታን ለመለየት እና ቅድመ ምህንድስና ጥናቶችን ለማካሄድ የተጠቃሚዎችን ዝርዝር ያዘጋጃል ሲል መግለጫው አክሏል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኑክሌር ኃይልን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም ትብብርን በማሳደግ ላይ መሆናቸውንና ሮሳቶም ኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይልና የኃይል ነክ ያልሆኑ ፕሮግራሞችን በማሳደግ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ገልፀዋል።“የተፈረመው ስምምነት እና ሮሳቶም የኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኑክሌር ሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ማእከልን በኢትዮጵያ ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ብቸኛ አቅራቢ ሆኖ መመረጡ ሀገራቶቻችን የረጅም ጊዜ ትብብርን ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት በድጋሚ ያረጋግጣል" ሲሉ የኩባንያው ክፍል ኃላፊ ኢልያ ቬርጊዛኤቭ መግለጻቸውን ሮሳቶም ጠቅሷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0