ብሪክስ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ዕድገት ለማፋጠንና በዓለም አቀፍ መድረክ ያለውን አሰላለፍ በማስተካከል ሚዛን ለመጠበቅ ያግዛል ተባለ

ሰብስክራይብ
ብሪክስ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ዕድገት ለማፋጠንና በዓለም አቀፍ መድረክ ያለውን አሰላለፍ በማስተካከል ሚዛን ለመጠበቅ ያግዛል ተባለ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትብብርን ለማጠናከር ጠቃሚ ያደርጋታል ያሉት በኢትዮጵያና የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራኢ ናቸው። አምባሳደሩ አክለውም በብሪክስ ማዕቀፍ ህንድ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ማሻሻያ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የልማት ትብብርና ሌሎች ግንኙነቶችን ለማጠናከር ብሪክስ ትልቅ ዕድል ይዞ መምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡በተጨማሪም አምባሳዳሩ በልማት ሥራዎች የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ በዕውቀትና ስትራቴጂ በትብብር በመሥራት ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ህንድ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች ማለታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡አምባሳደር አኒል ኩማር ራኢ በስተመጨረሻም  ብሪክስ ኢትዮጵያ ከህንድና ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ትብብርና አጋርነትን ለማጠናከር፣ ልምድና ዕውቀትን በመለዋወጥ ለመሥራት እንደሚያስችላት አመላክተዋል፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0