የናይጄሪያው ፖርት ሀርኮርት ማጣሪያ  ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት ሥራ መጀመሩ በኃይል እራስን ለመቻል አንድ እርምጃ መሆኑን የናይጄሪያ ብሄራዊ ነዳጅ ኩባንያ የስራ ኃላፊ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የናይጄሪያው ፖርት ሀርኮርት ማጣሪያ  ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት ሥራ መጀመሩ በኃይል እራስን ለመቻል አንድ እርምጃ መሆኑን የናይጄሪያ ብሄራዊ ነዳጅ ኩባንያ የስራ ኃላፊ ተናገሩ“ዛሬ የፖርት ሀርኮርት የነዳጅ ማጣሪያ በይፋ ድፍድፍ ነዳጅ ማጣራት መጀመሩ ለናይጄሪያ ትልቅ ስኬት ነው። ይህ ፈርቀዳጅ ውጤት ለሀገራችን በኃይል ራሷን የመቻል እና ለኢኮኖሚ እድገት አዲስ ዘመንን ያመለክታል” ሲሉ የናይጄሪያ ብሄራዊ ነዳጅ ኩባንያ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ የሆኑት ኦሉፌሚ ሶኔዬ መግለጻቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።እንደ ሶኔዬ ገለፃ ማጣሪያው  በ 60 በመቶ አቅሙ እየሰራ ሲሆን በቀን 60,000 በርሜል ድፍድፍ ዘይት በማጣራት ላይ ነው። በዚህም የጭነት መኪናዎች ጭነት ሥራዎች ቀድሞውኑ በመካሄድ ላይ ናቸው ብለዋል።ኩባንያው ዋሪ የዘይት ማጣሪያ  ለማደስ በንቃት እየሰራ መሆኑንም ሃላፊው ለዘኔሽን ጋዜጣ ጠቁመዋል።"ለፕሬዚዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ፣ ለኩባንያው የቦርድ አባላት እና ኩባንያው ግሩፕ ዋና ስራአስፈፃሚ ሜሌ ክያሪ፣ ለዚህ የለውጥ ፕሮጀክት ላሳዩት የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንኳን ደስ አላችሁ። አብረን የናይጄሪያን የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታን እየቀየርን ነው!" በማለት ደምድመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0