የሊባኖስ ባለሥልጣናት በነገው እለት ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ምንጭ ገለፀ

ሰብስክራይብ
የሊባኖስ ባለሥልጣናት በነገው እለት ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ምንጭ ገለፀ“ስምምነቱ ስኬታማ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ በሊባኖስ በኩል በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ወስጥ ምናልባትም ረቡዕ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ይፋ ያደርጋሉ” ሲል ሰኞ ዕለት ምንጩ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።ስምምነቱ በሊባኖስ የቀድሞው መሪ ሚሼል አውን ከስልጣን ከወረዱበት ከጎርጎሮሳውያኑ 2022 መገባደጃ ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ ያልተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማቆየትንም ያካትታል።ባሳለፍነው ማክሰኞ በመካከለኛው ምስራት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ አሞስ ሆችስተይን ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ አሜሪካ ያቀረበችውን ሀሳብ አስመልክቶ የሊባኖስን እና ሄዝቦላህን አቋም ለመስማት ቤሩት ተገኝተው ነበር።ከሊባኖስ ፓርላማ አፈ ጉባዔ ነቢህ ቤሪ ጋር በተደረገው ውይይት የተወሰነ መሻሻል መታየቱን ሆችስተይን ረቡዕ ዕለት  ተናግረዋል። ከቤሩት ጉብኝት በኋላ ሆችስታይን በቴል አቪቭ ንግግሮችን አድርገዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0