የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በዳይመንድ ላይ የተጣለባቸው እግድ እንዲነሳ የረዷቸውን የሩሲያን መሪዎች አመሰገኑ እንደ ሩሲያ ኤምባሲ ገለፃ

ሰብስክራይብ
የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በዳይመንድ ላይ የተጣለባቸው እግድ እንዲነሳ የረዷቸውን የሩሲያን መሪዎች አመሰገኑ እንደ ሩሲያ ኤምባሲ ገለፃ ባለፈው ህዳር 15 በዱባይ በተደረገው እና  የዳይመንድ ንግድ እገዳው እንዲነሳ በነበረው የኪምበርሌ ሂደት ቅደመ  ስብስባ ወቅት ፕሬዚዳንት ፋዩስቲን አርቼንጅ ቶዩድራ ለፕሬዚዳንት ቭላድሚን ፑቲን እገዳው እንዲነሳ ላደረጉት እርዳታ ምስጋና መላካቸውን በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሩሲያ ኤምባሲ በመግለጫው አስታውቋል። ቶዩድራ እንዳስረዱት የሩሲያው የፋይናንስ ሚኒስቴር አንቶን ሲሉአኖቭ ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል ፤ የሩሲያ የፋይናንስ ሚኒስቴር ሰራተኞች ፣ በማእከላዊ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የሩሲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሁሉም በማእከላዊ አፍሪካ ሰላም እና ፀጥታ እንዲሰፍን ድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ አድርሰዋል። "በማእከላዊ አፍሪካ ላይ ተጥሎ የነበረው  የከበሩ ድንጋዩች ንግድ እገዳ መነሳቱ ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚ እድገት ልማት እና የማእከላዊ አፍሪካ ዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተሻለ ሁኔታን ይፈጥራል" በማለት ኤምባሲው ትኩረት ሰጥቶበታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0