🪖 ፕሬዚዳንት ትራምፕ 15,000 ትራንስጀንደር (የተወለዱበትን ፆታ የቀየሩ) የጦሩ አባላት በአዲስ ህግ ያሰናብቷቸዋል ተባለ 

ሰብስክራይብ
🪖 ፕሬዚዳንት ትራምፕ 15,000 ትራንስጀንደር (የተወለዱበትን ፆታ የቀየሩ) የጦሩ አባላት በአዲስ ህግ ያሰናብቷቸዋል ተባለ  ወታደራዊ ምንጮቹን ጠቅሶ የብሪቲሽ ጋዜጣ እንደዘገበው ፤ ትራምፕ ይህንን ህግ እግራቸው ኋይት ሀውስን እንደረገጠ ያፀድቁታል ተብሎ ይጠበቃል። የፆታ ቅየራ ያደረጉ የጦሩ አባላት ከጤና ጋር በተያያዘ ለአገልግሎት ብቁ አይደሉም በሚል እንደሚሰናበቱ ጋዜጣው አስረድቷል።አሁን ላይ የአሜሪካ ጦር አዳዲስ አባላትን ሲመለምል ችግር እያጋጠመው እንደሆነ የትራምፕን እቅድ የሚያውቁት ወታደራዊ ምንጭ  መናገራቸውን ሪፖርቱ በአፅንኦት ዘግቧል። አዲሱ የትራምፕ ትእዛዝ የፆታ ቅየራ ያደረጉ ሰዎች ከማንኛውም አይነት የጦር አገልግሎት የሚያግዳቸው ይሆናል። ከዚህ ቀደም ብሎ በስም ያልተጠቀሱ ምንጮች ዋቢ በማድረግ ሚዲያዎች እንደዘገቡት የአሜሪካ መከላከያ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ኋይት ሀውስ ከመግባታቸው በፊት ለፕሬዚዳንቱ በሚመች መልኩ የጦር እርከኖችን እያስተካከለ እና አላስፈላጊ የሆኑትን እያስወገደ ይገኛል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0