የሩሲያ እና ቱርክ ፕሬዝደንቶች የኢኮኖሚ ትብብራቸውን አስመልክቶ የስልክ ውይይት አደረጉ

ሰብስክራይብ
  የሩሲያ እና ቱርክ ፕሬዝደንቶች የኢኮኖሚ ትብብራቸውን አስመልክቶ የስልክ ውይይት አደረጉ " በጎርጎሮሳዊያኑ ጥቅምት 23 በካዛን ከተደረገው የብሪክስ ጉባኤ ጉን ለጎን የነበረውን የሁለትዩሽ ውይይትን በማስቀጠል ፦  የተጀመረውን የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብርን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል" በማለት በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ረሲብ ታይቡ ኤርዶዋን መካከል የተደረገውን ውይይት ውጤት የክሬሚሊን መግለጫ አትቷል። በስልክ ውይይቱ ወቅት የቱርኩ መሪ  የቀጠናው ውጥረት እንዲያበቃ ቱርክ የራስዋን ሚና መውጣቷን እንደምትቀጥል እና አንካራ 'ለሰላም ሂደቱ የራስዋን ድርሻ እንደምትወጣ' አፅንኦት ሰጥተውበታል በማለት የክሬሚሊን መግለጫ አስረድቷል ።መግለጫው አክሎም መሪዎቹ በተለያዩ አለምአቀፍ ጉዳዮች ላይ አውርተዋል ብሏል። " ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ቱርክ እና ሩሲያ በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ አላማ አላቸው ፤ በተለይም የንግድ እንቅስቃሴዎች በማሳደግ" በማለት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በኤክስ አካውንቱ ፅፏል።ባለፈው ጥቅምት ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን በካዛን የተደረገውን የብሪክስ ጉባኤ የተካፈሉ ሲሆን በወቅቱ ፑቲንን ጨምሮ ከተለያዩ መሪዎች ጋር የጎንዩሽ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት የሩሲያ እና ቱርክ ሀላፊዎች ብዙ ጉዳዩችን ያነሱ ሲሆን የሁለቱ ሀገራት የጋራ ግንኙነት፣ በዩክሬን ያለው ግጭት እና የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዩች ይጠቀሳሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0