የህዳር 16 ረፋድ  አበይት የዓለም  ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የህዳር 16 ረፋድ  አበይት የዓለም  ዜናዎች፦ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት የአበዳሪዎች እና የፋይናንስ ኃላፊዎች ኮንፈረንስ እያስተናገዱ ሲሆን ውይይቱ የ 12.7 ቢሊዮን ዶላር የብድር ክምችት ለመክፈል እና የአገሪቱን የውጭ ብድር ዳግም ለማደራጀት  የሚያስችል ነው። ይህም ዚምባብዌ ከሃያ ዓመታት በላይ በኋል ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዓለም አቀፍ የካፒታል ገበያ እንድትገባ ለማስቻል ያለመ ነው። የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ቴቦኔ 4.5 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ያመጣል የተባል ለጎርጎሮሳዊያኑ 2025 በጀት ሕግ ላይ ፊርማቸውን ማሳረፋቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። እሁድ ዕለት ዛምቢያ እና ዚምባብዌ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ብልሽት እያጋጠመ ባለበት ወቅት ከበርካታ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ማሳለፋቸውን የኃይል ኩባንያዎች ገልጸዋል። አክለውም የኃይል የተቋረጠበት መንስዔ አለመታውቁን ጠቅሰዋል። በሊቱዌኒያ የዲኤችኤል ሎጂስቲክስ ኩባንያ አውሮፕላን ላይ የደረሰው የመከስከስ አደጋ "በቴክኒክ ችግሮች" ምክንያት ሊሆን ይችላል በሚል  እየተጣራ መሆኑን መገናኛ ብዙኃን የክራይስስ ማኔጅመንት ማዕከልን ጠቅሰው ዘግበዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በአንድ ምሽት 23 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማውደሙን  አስታውቋል። እስራኤል በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ  ቅደመ-ፍቃድ መስጠቷን  ይኔት የዜና አውታር  ዘግቧል። ዶናልድ ትራምፕ "ሴቭ አሜሪካ" የተሰኘው አዲስ መጽሐፋቸው መሸጥ መጀመሩን አስታውቀዋል፤ መጽሐፉ የፕሬዝዳንትነታቸውን የመጀመሪያዎቹን አራት ዓመታትና በቀጣዩ የዋይት ሃውስ የሥልጣን ዘመን ቆይታቸው ያላቸውን ራዕይ ይገልጻል። 75 ኩቢት ኳንተም ኮምፒውተር በሚቀጥለው ዓመት በሩሲያ ሊፈጠር እንደሚችል የሩሲያ መንግስት ኮርፖሬሽን ሮሳቶም ኃላፊ  አማካሪ ሩስላን ዩኑሶቭ  ገለጹ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0