ትራምፕ የዩክሬን ግጭት መባባሰ ' በጣም አሳስቧቸዋል' የተመራጩ ፕሬዝዳንት የፀጥታ አማካሪ

ሰብስክራይብ
ትራምፕ የዩክሬን ግጭት መባባሰ ' በጣም አሳስቧቸዋል' የተመራጩ ፕሬዝዳንት የፀጥታ አማካሪ " ተመራጩ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ግጭት መባባስ እና ወዴት እንደሚያመራ አሳስቧቸዋል" በማለት የኮንግረስ አባሉ ማይክ ዋልትዝ የግጭቱን መባባስ አስመልክቶ የፕሬዝዳንቱን ሀሳብ ለፎክስ የዜና ወኪል ትላንትና ገልፀዋል። ዋልትዝ አክለውም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባንደን አስተዳደር ዩክሬን የሩሲያን ግዛት እንድትደበድብ ፍቃድ መስጠታቸው እንዲሁም የሩሲያ ኦርሽኒክ ተብሎ በሚጠራው ሚሳኤል ምላሽ መስጠት ግጭቱን 'በግልፅ ያባባሰ' እንደሆነ እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህ ግጭት እንዲቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት አስታውሰዋል። ዋልትዝ የግጭቱ ተሳታፊዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ በጣም አሳሳቢ ነው ብለዋል። አክለውም የሰሜን ኮርያ ናቸው የተባሉ ወታደሮች በግጭቱ መሳተፍ የደቡብ ኮርያን በግጭቱ ለመሳተፍ ማስብ እያሳሳበ እንደሆነ እና የአሜሪካ አጋር ሀገሮች " ያላቸውን የሚሳኤል አቅርቦት እያሳደጉ ነው በማለት ገልፀዋል። " ይህንን ግጭት በሀላፊነት እንዲቆም ማድረግ አለብን።  የእርስበርስ መጠራጠር እንዲቆም ማድረግ ፣ ሰላምን መመለስ አለብን እንዲሁም  ግጭቱን እንዳይባባስ ምላሽ መስጠት ማቆም አለብን" በማለት ዋልትዝ ተናግረዋል። በትላንትናው እለት ቀደም ብሎ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ተሰናባቹ የባይደን አስተዳደር የዩክሬን ግጭት ተባብሶ እንዲቀጥል የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው ብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0