የሩሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለውጭ ሀገር ተማሪዎች 'ተመራጭ ናቸው' :  የቋንቋ ችግርም ከትምህርታቸው አያስተጓጉላቸውም ዛምቢያዊዉ ተማሪ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለውጭ ሀገር ተማሪዎች 'ተመራጭ ናቸው' :  የቋንቋ ችግርም ከትምህርታቸው አያስተጓጉላቸውም ዛምቢያዊዉ ተማሪ " የሩሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጡት ድግሪም ሆነ ዲፕሎማ በአለም ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ሲሆን ፤ ያለ ተጨማሪ ፈተና ስራ እንደስራ ስለሚያደርገን ይሄ ደግሞ ጥሩ ነገር ነው" ፤ ይህንን ያለው ከተለያዩ አግራሪያን ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ስድስት የግብርና ተማሪዎችን በሚያሳትፈዉ ፣ 'ኢንተርን' የተሰኘው የግብርና ሪያሊቲ ሾው ላይ መሳተፍ የቻለው እና በሩሲያ የግብርና ኢንተርፕራይዝ ውስጥ ልምምድ ላይ ያለው  የኩባን አግራሪያን ዩንቨርስቲ የእንስሳት ህክምና ተማሪው ጢሞቲ ዙሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጠው አስተያየት ነው።።ተማሪው አክሎምም ይህ የሪያሊቲ ሾው የእውቀት ሽግግር የታየበት እንዲሁም የእንስሳት ህክምናን በተመለከ የስራ ልምድ የተለዋወጡበት እና ከመስል ባለሙያዎች ጋር ጠንካራ የሆነ ግንኙነት የፈጠረለት ነው። " የእንሰሳት ሀኪም ሆኜ ወይም ልምድ ያላቸው ሀኪሞች ጋር ሆኜ ከእንሰሳት ጋር እየሰራሁ ነው። ይህ ሾው እንሰሳትን ማከም ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው እንዴት መኖር እንዳለብኝ አስተምሮኛል" በማለት ከሪያሊቱ ሾው ያገኘውን ልምድ ተናግሯል ።የሩሲያን ቋንቋ ለመማር ያጋጠመውን አስቸጋሪ ሁኔታ የፈታበትን መንገድ ሲያስረዳ  ፦ በዛምቢያ መዲና ሉሳካ ባለው የሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማእከል ውስጥ የሚሰጡ የቋንቋ ትምህርቶች መውሰድ መሆኑን ተናግሮ የትምህርቶቹን አስፈላጊ መሆን አፅንኦት ሰጥቶበታል። "እድለኛ ነበርኩ ሀገር ቤት እያለሁ ሩሲያኛ መማሬ። በትንሹ የቋንቋውን መሰረታዊ ነገሮች ማግኘት ችዬ ነበር። በሉሳካ ያለው ማእከል ከአላማዎቹ መካከል አንዱ እዚህ መጥተው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የቋንቋዉን መሰረታዊ ነገሮች ማስያዝ ነው" በማለት ዙሉ አስረድቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0