የሩሲያ የሳይበር ደህንነት ግዙፉ ኩባንያ ካስፐርስካይ እና አፍሪፖል የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል ጥምረታቸውን አጠናከሩ

ሰብስክራይብ
 የሩሲያ የሳይበር ደህንነት ግዙፉ ኩባንያ ካስፐርስካይ እና አፍሪፖል የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል ጥምረታቸውን አጠናከሩባለፈው ሳምንት በአልጀርስ የካስፐርስካይ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩጌኔ ካስፐርስካይ እና የአፍሪፖል ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ጃሌል ቼልባ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት የበለጠ ለማጠናከር የሳይበር ወንጀልን ለመከላከልና ለመዋጋት  የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ስምምነቱ ለኩባንያው እና ለአፍሪካ ህብረት ሕግ አስፈጻሚ ድርጅት የቅርብ ጊዜ የሳይበር ወንጀል እንቅስቃሴን በተመለከተ አስጊ መረጃን ለመለዋወጥ ህጋዊና እና ቀላል ያደርገዋል።በኩባንያው መግለጫ መሰረት አፍሪካ ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር ካስፐርስካይ ሶሉሽንስ የሳይበር ወንጀሎችን የተከላከለበት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢንዱስትሪያል ቁጥጥር ስርዓቶች የተጫኑባቸው ኮምፒውተሮች አሏት። “ከአፍሪፖል ጋር ያለንን ትብብር በማሳደግ እና ለሚከሰቱ የሳይበር አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስፈልጉትን መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ለኤጀንሲው በማሟላት፤ ለበለጠ የሳይበር መቋቋም እና ለሁሉም ደህንነቱ የተጠበቀ ሳይበርስፔስን በማጎልበት ረገድ አስተዋፅኦአችንን ለማሳደግ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል ካስፐርስካይ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0