አጋር የሩሲያ ማዕከል በሴራሊዮን ተከፈተ

ሰብስክራይብ
አጋር የሩሲያ ማዕከል በሴራሊዮን ተከፈተ በሴራሊዮን የሚገኘው የሩሲያ ማዕከል መክፈቻ፤ የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የንግድ፣ የጤና አገልግሎት እና ማህበራዊ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት፤ በይፋዊ ሥነ-ሥርዓት አርብ እለት መካሄዱን የሩሲያ የሰብዓዊ ትብብር ኤጀንሲ ሮስትሩድኒቼስትቮ ለስፑትኒክ ተናግሯል። በሩሲያ የሴራሊዮን አምባሳደር ሞሐመድ ዮንጋዎ፤ ለአዲሱ የሩስያ ማዕከል መከፈት ትልቅ ሚና እንደተጫወቱ ተገልጿል። የሀገሪቱ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ኬንዬ ባርሌይ እና የማዕድንና ማዕድን ሀብት ሚኒስትር ጁሊየስ ዳንኤል ማታይ በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ለተጋባዥ እንግዶች ንግግር አድርገዋል። ዶ/ር ባርሌይ "ይህ ለሀገራችን ትልቅ አጋጣሚ ነው፤ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር በመቻላችን በጣም ደስተኞች ነን" ብለዋል። "በፕላን እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ትብበር ለማስፋት እንሰራለን፤ የሀገራችንን እድገት እና ልማት ለማጠናከር ከሩሲያ ህዝብ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነን" ሲሉም አክለዋል። ምስሎቹ ከሩሲያ የሰብዓዊ ትብብር ኤጀንሲ የተገኙ ናቸው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0