ሩሲያ የፆታ ለውጥ የሚፈቅዱ ሀገራት ዜጎች ህጻናትን በጉዲፈቻ እንዳይወስዱ ከለከለች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ የፆታ ለውጥ የሚፈቅዱ ሀገራት ዜጎች ህጻናትን በጉዲፈቻ እንዳይወስዱ ከለከለች የሩሲያ ህጻናት፤ በሕክምና ጣልቃ ገብነት የፆታ ለውጥ ማድረግ የሚፈቀድባቸው ሀገራት ዜጎችን ጉዲፈቻ ወይም ሞግዚትነት የሚከለክል ማሻሻያ በሩሲያ የቤተሰብ ሕግ ላይ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል። ይህም ተገቢው የሕክምና ጣልቃ ገብነት ሳይኖር በውጭ ሀገር ዜጎች የመታወቂያ ሰነዶች ላይ ጾታን መለወጥ ያካትታል። በተጨማሪ፤ በበይነ መረብ፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በፊልም እና በማስታወቂያ ላይ “ከልጆች ነፃ አስተሳሰብ” ፕሮፓጋንዳ የሚከለክለውን ህግ ፑቲን ቅዳሜ እለት ፈርመዋል። በህጉ መሰረት የሩሲያ ባለስልጣናት ህፃናትን ከዚህ ርዕዮተ ዓለም ለመጠበቅ እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0