ኔታንያሁን በማሰር አይሲሲን የሚረዱ የአሜሪካ አጋሮች ማዕቀብ ይጠብቃቸዋል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር አስፈራሩ

ሰብስክራይብ
ኔታንያሁን በማሰር አይሲሲን የሚረዱ የአሜሪካ አጋሮች ማዕቀብ ይጠብቃቸዋል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር አስፈራሩ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን በቁጥጥር ስር በማዋል፤ ዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመርዳት በሚሞክሩ የአሜሪካ አጋሮች ላይ፤ ማዕቀብ እንጥላለን ሲሉ የሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተር ሊንድሲ ግራሃም አስጠንቅቀዋል። "ለማንኛውም አጋር - ካናዳ፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ - አይሲሲን ለመርዳት የምትሞክሩ ከሆነ ማዕቀብ እንጥልባችኋለን" ሲሉ ፎክስ ኒውስ ላይ ተናግረዋል። ስለማዕቀቦቹ ምንነት የተጠየቁት ግራሃም፤ ዩናይትድ ስቴትስ የአይሲሲን የእስር ትዕዛዝ የሚደግፉ ሀገራትን ኢኮኖሚ "ማድቀቅ" አለባት ሲሉ ማስፈራሪያቸውን አጠናክረዋል። ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በጋዛ ሰርጥ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ያለው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፤ ሐሙስ እለት የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል። እስራኤል፤ አይሲሲ ጉዳዩን የመመልከት ስልጣን የለውም በሚል ያቀረበችው ተቃውሞ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። እስራኤል፤ አይሲሲ ፍልስጤምን የሚመለከቱ ሁሉንም ጉዳዮች የማየት ስልጣን የለውም በማለት በተደጋጋሚ ተከራክራለች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአይሲሲን ውሳኔ “አስደንጋጭ” ሲሉ ገልጸውታል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0