የኢትዮጵያን እድገት የሚያሳይ ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ በ3ኛው ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፤ ኢትዮጵያ ከማዕድን ሀብቷ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እንደምትሠራ ተናግረዋል። የሀገሪቱን ከፍተኛ የማዕድን አቅም እንዲኹም አዲሱን የመንግሥት የማዕድን ፓሊሲ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የማዕድን ሀብትን ለሀገራዊ ልማት መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። ከህዳር 14-17 በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ሚንትክስ 2024 ኤክስፖ፤ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የማዕድን ኩባንያዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ምሑራንን እና ዲፕሎማቶችን አሰባስቧል። ኢትዮጵያ ካላት ከፍተኛ የማዕድን ሃብት አንፃር፤ መንግሥት ለማዕድን ዘርፍ ቅድሚያ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን፤ ኤክስፖው የዘርፉን እምቅ አቅም በማሳየት እና ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ዓለም አቀፍ የገበያ አማራጭ በማቅረብ፤ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ታልሞ የተዘጋጀ ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያን እድገት የሚያሳይ ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ
የኢትዮጵያን እድገት የሚያሳይ ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያን እድገት የሚያሳይ ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ በ3ኛው ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፤ ኢትዮጵያ ከማዕድን ሀብቷ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ... 23.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-23T19:28+0300
2024-11-23T19:28+0300
2024-11-23T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያን እድገት የሚያሳይ ዓለም አቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ
19:28 23.11.2024 (የተሻሻለ: 19:44 23.11.2024)
ሰብስክራይብ