ገዥው የኢትዮጵያ ፓርቲ ብልፅግና 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ የብልጽግና ፓርቲ የተቋቋመበትን አምስተኛ ዓመት አሰመልክቶ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፤ ፓርቲው ፈተናዎች ቢገጥሙትም በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ዕድገት እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ ጉልህ ስኬቶችን እንዳስመዘገበ አንስተዋል። ፓርቲው የተመሰረተበትን መርሆች የዘረዘሩት ባለስልጣኑ፤ ሀገራዊ ጉዳዮችን ለመፍታት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራርነት የተመሰረተው ፓርቲ አንድነትን፣ ብሔራዊ ስሜትን እና አካታችነትን በማዳበር፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በክብርና በደስታ የሚኖርበት ማህበረሰብ የመፍጠር ዓለማ እንዳነገበ ተናግረዋል። የፓርቲው ስኬት በጠንካራ ስራ፣ በቆራጥ አመራር እና በህዝብ ድጋፍ የተመዘገበ ነውም ብለዋል። የፖለቲካ ምህዳርን ማስፋት፣ ሀገራዊ ትርክት መፍጠር፣ ትክክለኛ የፌደራሊዝም ስርዓት መመስረት እና ምርታማነት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚጠቀሱ የብልፅግና ፓርቲ ስኬቶች እንደሆኑም አደም ፋራህ ጠቁመዋል። እንደ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የስንዴ ምርት፣ የኮሪደር ልማት እና የማህበራዊ አገልግሎት ተነሳሽነቶች ሌላው የፓርቲው ስኬቶች ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያን የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና የብሪክስ አባልነት የጠቀሱት አደም ፋራህ፤ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ተፅዕኖዋ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ገዥው የኢትዮጵያ ፓርቲ ብልፅግና 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ
ገዥው የኢትዮጵያ ፓርቲ ብልፅግና 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ
Sputnik አፍሪካ
ገዥው የኢትዮጵያ ፓርቲ ብልፅግና 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ የብልጽግና ፓርቲ የተቋቋመበትን አምስተኛ ዓመት አሰመልክቶ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፤ ፓርቲው ፈተናዎች ቢገጥሙትም በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ... 23.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-23T18:11+0300
2024-11-23T18:11+0300
2024-11-23T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий