የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሞሮኮ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገቡ ፕሬዝዳንቱ ከብራዚል መልስ በሞሮኮ ካዛብላንካ ከተማ ሐሙስ እለት አጭር ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፤ ከልዑል ሙላይ ሀሰን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አካሃኑች ጋር ተገናኝተዋል። የሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት በትክክለኛ መንገድ ላይ እንደሆነ የጠቀሱት ሺ፤ በተለያዩ ዘርፎች ፍሪያማ እና ንቁ ትብብር እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 ንጉስ ሞሐመድ ስድስተኛ በቻይና ያደረጉትን ጉብኝት በማስታወስ፤ የቻይና እና ሞሮኮን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደረሰ እንደሆነ ተናግረዋል። በቅርቡ ቤጂንግ ውስጥ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም እና በቻይና-አረብ ሀገራት የትብብር መድረክ የተገኙ ውጤቶችን ተግባራዊ ለማድረግ፤ ቻይና ከሞሮኮ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት ሺ አፅንዖት ሰጥተዋል። በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ተጨማሪ የትብብር መስኮች ሊኖር እንደሚችልም አመላክተዋል። ልዑል አልጋ ወራሽ ሀሰን በበኩላቸው፤ የንጉስ ሞመመድ ስድስተኛን መልከም ምኞት ያስተላለፉ ሲሆን፤ በሞሮኮ የመሠረተ ልማት እና የባቡር ዘርፍ እየጨመረ የመጣው የቻይና ኢንቨስትመንት የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማነቃቃቱን ጠቅሰዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሞሮኮ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገቡ
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሞሮኮ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገቡ
Sputnik አፍሪካ
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሞሮኮ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገቡ ፕሬዝዳንቱ ከብራዚል መልስ በሞሮኮ ካዛብላንካ ከተማ ሐሙስ እለት አጭር ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፤ ከልዑል ሙላይ ሀሰን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አካሃኑች... 23.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-23T16:33+0300
2024-11-23T16:33+0300
2024-11-23T17:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሞሮኮ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገቡ
16:33 23.11.2024 (የተሻሻለ: 17:14 23.11.2024)
ሰብስክራይብ