አዲሱ የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚመሩ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
አዲሱ የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚመሩ ተናገሩ የቀድሞውን መንግሥት የኢኮኖሚ አያያዝ ኦዲት እንደሚያደርጉ ቃል የገቡት ተመራጩ የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቪን ራምጎላም፤ የገንዘብ ሚኒስትርነቱን ቦታ ራሳቸው እንደሚይዙ ተናግረዋል። "ተሰናባቹ መንግሥት ያደረሰውን ጉዳት ለመመርመር ኢኮኖሚውን ኦዲት እያደረግን ነው" ሲሉ የካቢኔ ሹመታቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የራምጎላም ጥምር መንግሥት ከ62 የብሔራዊ ምክር ቤት መቀመጫዎች 60 የሚሆነውን በማሸነፍ ወሳኝ ድል ተጎናጽፏል። የመንግሥትን ፋይናንስ ኦዲት ለማድረግ እና በቀደመው የስልጣን ዘመናቸው (1995-2000 እና 2005-2014) የጀመሩትን የኢኮኖሚ አማራጮችን የማስፋት ጥረት ለማስቀጠል እንዳቀዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0