ጁባ ውስጥ ሐሙስ የተሰማው የተኩስ ልውውጥ በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት እንደተከሰተ የደቡብ ሱዳን ጦር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ጁባ ውስጥ ሐሙስ የተሰማው የተኩስ ልውውጥ በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት እንደተከሰተ የደቡብ ሱዳን ጦር አስታወቀ የደቡብ ሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ሉል ሩዋይ ኮአንግ፤ ሐሙስ አመሻሽ በጁባ ቶንግፒኒ የመኖሪያ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የስለላ ሀላፊ ጀነራል ኩር መኖሪያ አቅራቢያ ከባድ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ለሱዳን ፖስት ተናግረዋል። የተኩስ ልውውጡ ከቀድሞው የብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊ መታሰር ጋር የተያያዘ ነው በማለት ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የሰሩትን ዘገባ የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ አስተባብለዋል። ጄኔራል አኮል ኩር እንዳልታሰሩ እና በተኩስ ልውውጡ ወቅት መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንደቆዩ ገልጸዋል። የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ አክለውም፤ አለመግባባቱ የተፈጠረበት ምክንያት አለመታወቁን ተናግረዋል። "ሁለት ወታደሮች በጥይት ተመተው ቆስለዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዥ ጄኔራል ሳንቲኖ ዴንግ ወል በፍጥነት ወደ ስፍራው በመሄድ ግጭቱ እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጥተው ሁኔታውን መቆጣጠር ችለዋል" ያሉት ቃል አቀባዩ፤ "በተፈጠረው ሁኔታ ዙርያ ነገ ምርመራ እንደሚጀመር" ጠቁመዋል። ሜጀር ጄኔራል ኮአንግ፤ ሁኔታው ​​በቁጥጥር ስር መዋሉንም ለአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0