የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሩሲያ ምዕራባውያን ለኪዬቭ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምላሽ መስጠት እንደምትችል ያሳያችበት እንደሆነ አንድ ባለሙያ ተናገሩ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የደህንነት እና ልማት ጥናት ኤክስፐርት እና የምርምር ባልደረባ ዶ/ር ሌጀንድ አሱሊም፤ ሩሲያ ያካሄደችው የኦሬሽኒክ መካከለኛ ርቀት ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ብዙ አንደምታ ያለው አደገኛ ሁናቴ ነው ብለዋል። “ምዕራባውያን ሩሲያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዳታገኝ እና እንዳትድግ ለመደናቀፍ ማዕቀቦችን እየጣሉ ባለበት ሰዓት አዳዲስ የጦር መሣሪያዎችን መጠቀሟ ጠንካራነቷን የሚያሳይ ነው" ሲሉ ዶ/ር አሱሊም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። “ሩሲያ የምዕራቡ ዓለም ለዩክሬን ለሚደረገው ድጋፍ ተመጣጣኝ ምላሽ የመስጠት አቅም መፍጠሯን ያመላክታል" ሲሉም ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል። ሞስኮ በግዛቷ አቅራቢያ ወይም በግዛቷ ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፤ ኔቶ ለዩክሬን እርዳታ ከመስጠት ባለፈ ቀጥተኛ የውክልና ጦርነት ውስጥ እየተሳተፈ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው ማለቷን አጠናክረው ተናግረዋል። “ይህ ለሩሲያ ብዙ የደህንነት ስጋቶችን ይፈጥራል። በተለይም በምስራቅ አውሮፓ የኔቶ ወታደራዊ አሻራ እያደገ መምጣቱ እና ዩክሬንን በማስታጠቅ ላይ ያለው ተሳትፎ" ሲሉ አብራርተዋል። የጆ ባይደን አስተዳደር፤ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመመለሳቸው በፊት ጦርነቱን የማባባስ ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚችልም ኤክስፐርቱ ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ፤ ይህ አካሄድ “የተሳሳተ ስሌት፣ የድንበር ግጭት መስፋፋት እና ግጭቱን የማራዘም አደጋው ሰፊ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሩሲያ ምዕራባውያን ለኪዬቭ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምላሽ መስጠት እንደምትችል ያሳያችበት እንደሆነ አንድ ባለሙያ ተናገሩ
የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሩሲያ ምዕራባውያን ለኪዬቭ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምላሽ መስጠት እንደምትችል ያሳያችበት እንደሆነ አንድ ባለሙያ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሩሲያ ምዕራባውያን ለኪዬቭ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምላሽ መስጠት እንደምትችል ያሳያችበት እንደሆነ አንድ ባለሙያ ተናገሩ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የደህንነት እና ልማት ጥናት ኤክስፐርት እና የምርምር ባልደረባ ዶ/ር ሌጀንድ አሱሊም፤... 22.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-22T16:36+0300
2024-11-22T16:36+0300
2024-11-22T17:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሙከራ ሩሲያ ምዕራባውያን ለኪዬቭ ለሚያደርጉት ድጋፍ ምላሽ መስጠት እንደምትችል ያሳያችበት እንደሆነ አንድ ባለሙያ ተናገሩ
16:36 22.11.2024 (የተሻሻለ: 17:14 22.11.2024)
ሰብስክራይብ