ኢትዮጵያ ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ ልታወጣ ነው ተባለ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ ልታወጣ ነው ተባለየኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ፤ ለፓርላማ መርቷል። ረቂቅ አዋጁ የሀገሪቱን የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ ማጓጓዝ፣ ክምችት፣ መልሶ አጠቃቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት ያሲዛል ተብሏል። ለሀገሪቱ ፓርላማ የተመራው ረቂቅ አዋጅ፤ የዜጎችን በንጹሕ እና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ አለው ሲሉ፤ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ ተናግረዋል። አዋጁ ጸድቆ ሥራ ላይ ሲውል፤ በዜጎች ጤና እና በሥነ-ምህዳር ላይ ከባድ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ የሚገኘውን የፕላስቲክ ምርት ጉዳት ይቀንሳል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0