የሊቢያ የባለሙያዎች እና የኢንቨስትመንት ልዑክ በቅርቡ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኝ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
የሊቢያ የባለሙያዎች እና የኢንቨስትመንት ልዑክ በቅርቡ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኝ ተገለጸ የሊቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አል-ታሄር አል-ባኦር፤ በሊቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ሙሳ ጋር፤ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ዙርያ መክረዋል። ውይይቱ፤ የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ደቢባ በቅርቡ በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት የተገኙ ውጤቶች ላይ በተለይም፤ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ከፍተኛ ኮሚቴ እንደገና በማስጀመር ላይ ያተኮረ እንደነበር፤ የሊቢያ የዜና አውታር ዘግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሊቢያ ከተሞች የቀጥታ ጉዞ የሚጀምርበትን መንገድ እንዲሁም የኢትዮጵያን ኤምባሲ በትሪፖሊ በድጋሚ ስለመክፈት በውይይታቸው መክረዋል። የሊቢያ የባለሙያዎች ልዑክ እና የኢንቨስትመንት ኩባንያ ተወካዮች፤ በቅርቡ አዲስ አበባን በመጎብኘት ተጨማሪ የትብብር እድሎችን እንደሚፈትሹም፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያው አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ሙሳ ተናግረዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0