ቱርክ፤ ዩክሬን ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ ጥቃት እንድታደርስ በአሜሪካ የተሰጣትን ፍቃድ እንደማትቀበል ገለጸች

ሰብስክራይብ
ቱርክ፤ ዩክሬን ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ ጥቃት እንድታደርስ በአሜሪካ የተሰጣትን ፍቃድ እንደማትቀበል ገለጸች እርምጃው ዓለምን ወደ አዲስ የጦርነት አፋፍ ላይ ሊያቀርብ ይችላል፤ ሲሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶአን ተናግረዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ በሩሲያ ላይ የረዥም ርቀት የጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ መስጠታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሆኖም እስካሁን በይፋ የተሰጠ ማረጋገጫ የለም። ውሳኔው፤ "ምዕራቡ ዓለም ሩሲያ ላይ የከፈተው ጦርነት" እንዲባባስ የሚያደርገው ነው፤ ሲሉ ኤርዶአን አክለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0