ብራዚላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ቪኒሲየስ ጁኒየር የዘር ግንዱ ከካሜሩን እንደሚመዘዝ አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ብራዚላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ቪኒሲየስ ጁኒየር የዘር ግንዱ ከካሜሩን እንደሚመዘዝ አስታወቀ የሪያል ማድሪድ እና ብራዚል ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር፤ ቅድመ አያቶቹ ካሜሩናውያን እንደሆኑ፤ ብራዚል በትናንትናው እለት ከኡራጓይ ጋር ካደረገችው ጨዋታ በፊት አውቋል። የዲኤንኤ ምርመራው፤ የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን "ወርቃማው ዘሮች" ተነሳሽነት አካል ሲሆን፤ የብሔራዊ በድኑ ተጫዋቾች የዘር ግንዳቻውን ፈልገው እንዲያገኙ ለማድረግ የታለመ ዘመቻ ነው።ቪኒሲየስ፤ ከኡራጓይ ጋር ከተደረገው ጨዋታ በፊት የዘር ግንዱ ከአፍሪካ እንደሚመዘዝ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል። የዲኤንኤ ምርመራው፤ የእግር ኳስ ተጫዋቹ በእርሻ እና አንጥረኝነታቸው ከሚታወቁት የካሜሩን ቲካር ብሄረሰብ እንደመጣ አሳይቷል። የቲካር ብሄረሰብ መነሻ በጥንታዊው ምቡም ግዛት ውስጥ በነበረ የሥርወ-መንግሥት ግጭት ሲሆን፤ በክልሉ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ለመሆን ችሏል። የወርቃማው ዘሮች ዘመቻ፤ ከዘር ግንድ ሰርተፍኬት ባሻገር፤ በስፖርት ውስጥ ያለውን ዘረኝነትን ስለመዋጋት እና ልዩነቶችን ማክበር ላያ ያተኮረ እና ቪኒሲየስ ጁኒየርን የሚሳተፍበት ፊልም ለማውጣት አቅዷል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0