የህዳር 12 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የህዳር 12 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-🟠 የቀድሞው የጀርመን መራሄ መንግሥትአንጌላ ሜርክል ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ያደንቁ ነበር ማለታቸውን የጀርመን መገናኛ ብዙሃን ዘገበ።🟠 የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር የዩክሬንን 4.65 ቢልዮን ዶላር ዕዳ በከፊል ለመሰረዝ እንዳሰበ ተገለጸ።🟠 የአሜሪካ ሴኔት ለእስራኤል የጦር መሳሪያ አቅርቦትን ለመከልከል የቀረበውን ሃሳብ አገደ። ከ100 ሴናተሮች ውስጥ ከ 60 በላይ የሚሆኑት ሦስት ተዛማጅ የውሳኔ ሃሳቦችን የተቃወሙ ሲሆን 17 የህግ አውጭዎች ደግፈዋል፡፡🟠 እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሚገኘው ካማል አድዋን ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ባካሄደችው ጥቃት በትንሹ 66 ሰዎች መሞታቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።🟠 በአይስላንድ ሬይክጃንስ ልሳነ ምድር የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ጀመረ። ባለስልጣናት ነዋሪዎችን ከግሪንዳቪክ ከተማ ማስወጣታቸውን አስታውቀዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0