የህዳር 10 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የህዳር 10 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡- አለም የምትዳደርበት ሂደት መሻሻል ይኖርበታል ፤ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ ሪዩዲጄኔሮ ጂ-20 ጉባኤ ጎንዩሽ  ላይ የተናገሩት። የአፍሪካ ሀገራት እና ሌሎች አለምአቀፍ ማህበራት በጂ-20 ስብስብ ላይ ያላቸው ሚና ማደግ አለበት ፦ በጂ-20 መግለጫ ላይ እንደተፃፈው የሩሲያ መንግስት የሱዳንን ግጭት ለመፍታት  በዩናይትድ ኪንግደም እና ሴራሊዩን አማካኝነት ለተመድ የቀረበዉን የመፍትሄ ሀሳብ አትደግፍም ፤ ምክንያቱ ደግሞ የለንደን መንግስት በሀገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንድትገባ እድል ይሰጣል ያሉት በተመድ የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ምክትል የሆኑት ዲሚትሪ ፖለይንስክ ናቸው። ዩክሬን የረጅም- ርቀት ሚሳኤሎችን በሩሲያ ግዛት ላይ እንድትጠቀም አሜሪካን ፍቃድ መስጠቷል ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት በተመድ የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲልይ ንብንዘያ እንደተናገሩት ፤ ባይደን የሚያጡት ነገር አይኖርም ነገርግን ለንደን እና ፓሪስ አውሮፖን ብዙ መዘዝ ወዳለው ግጭት ጎትተው እያስገቧት ነው ብለዋል። ከሩሲያ መከላከያ ሚኒሰትር በተገኘ መረጃ መሰረት በዩክሬን እየተደረገ ባለው ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከተጀመረ ጀምሮ ከ900,000 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ያሳያል። የአሜሪካን መንግስት ለዩክሬን አዲስ ዙር የጦር መሳሪያ እርዳታ በቅርብ ቀን ሊያደርግ ነው ፤ በማለት በተመድ የአሜሪካን ቋሚ ተወካይ የተናገሩ ሲሆን የሚሰጠውን የእርዳታ ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል። የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ ከቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር በቻይና እና በሩሲያ መሀከል የተደረገውን ስምምነት ተግባራዊ ስለማድረግ እና ስለቀጣይ የጋራ እንቅስቃሴዎች መወያየታቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር አስታውቋል። የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን እንደያዙ ህገወጥ ስደተኞችን ለማስወጣት የጦር ሀይሉን እንደሚጠቀሙ እና በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚያውጁ አረጋገጡ።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0